በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በመተማ ወረዳ አንድ ሰው በታጣቂዎች ሲገደል ዘጠኝ እንደታገቱ ተገለጸ


በመተማ ወረዳ አንድ ሰው በታጣቂዎች ሲገደል ዘጠኝ እንደታገቱ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:44 0:00

በዐማራ ክልል በምዕራብ ጎንደር ዞን በመተማ ወረዳ ጉባይ ጀጀሊት በተባለ ቀበሌ፣ ታጣቂዎች፥ አንድ ሰው እንደገደሉና ዘጠኝ ሰዎችን አግተው እንደወሰዱ፣ የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ፡፡

ነዋሪዎቹ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ፣ ሐምሌ 1 ቀን 2015 ዓ.ም. በወረዳው፣ ከሽንፋ ተነሥቶ ወደ ገንዳዋ ቀበሌ እየተጓዘ የነበረን አንድ አይሱዚ ተሽከርካሪ፣ ጉባይ ጀጀሊት በምትባል ቀበሌ፣ በተለምዶ የልዩ ኀይል ካምፕ እየተባለ በሚጠራው ቦታ አስቁመው ተሳፋሪዎችን ከአስወረዱ በኋላ፣ አንድን ወጣት ሲገድሉ ዘጠኝ ሰዎችን ደግሞ አግተው ወደ ጫካ ይዘዋቸው ሔደዋል፡፡

ለታጋች ቤተሰቦችም ስልክ ደውለው፣ መጠኑ የተለያየ ብዙ መቶ ሺሕ የማስለለቂያ ቤዛ (ገንዘብ) እየጠየቁ እንደኾነ፣ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡

ነዋሪዎቹ፣ ለግድያው እና ለእገታው ተጠያቂ ያደረጉት፣ በጫካ የነበሩና በእርቀ ሰላም ስም ተመልሰው ወደ ማኅበረሰቡ የተቀላቀሉ ‘ጽንፈኛ’ ሲሉ የጠሯቸው፣ የቅማንት ታጣቂዎች እንደኾኑ አመልክተዋል፡፡

በወረዳው፣ ተደጋጋሚ የግድያ እና የእገታ ድርጊት እንደሚፈጸም የገለጹልን ሲሳይ የተባሉ ሌላ አስተያየት ሰጪ፣ በአካባቢው ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ፣ ከዐማራም ከቅማንትም ወገን የኾኑና “ሽፍታ” ሲሉ የጠሯቸው ኀይሎች መኖራቸውን ጠቅሰው፣ “ጥቃቱን ማስቆም አልቻሉም” ያሏቸውን የአካባቢውን የጸጥታ አካላት እና ባለሥልጣናት፣ ለጥቃቱ ተጠያቂ አድርገዋል፡፡

የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቢክስ ወርቄ፣ በተጠቀሱት የወረዳው አካባቢዎች፣ ግድያ እና እገታው መኖሩን አምነው፣ በሥፍራው ታጥቀው በሚንቀሳቀሱ ኀይሎች ላይ ርምጃ እየተወሰደ ነው፤ ብለዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG