በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአረብ ሊግ በሊቢያ ከበረራ ክልክል ቀጣናን ለማስከበር የተወሰደውን ርምጃ አፈጻጸም ነቀፈ


የአረብ ሊግ የሊቢያ የዓየር ክልል ከበረራ ነፃ እንዲሆን በጠየቀ በሳምንቱ አሁን የዓየር ጥቃቱን እየነቀፈ ነው።

ዛሬ የአረብ ሊግ ዋና ጸሐፊ አምር ሙሳ ሲናገሩ የተባበሩት መንግሥታቱ ለበረራ ክልክል ቀጣና ገቢራዊነት አረብ ሊግ ከፈለገው አልፎ የሄደ ነው ብለዋል።

አምር ሙሳ በካይሮ ለጋዜጠኞች ሲናገሩ ሊጉ የፈለገው ሲቪሎች ከጥቃት እንዲጠበቁ እንጂ በቦምብ እንዲደበደቡ አይደለም ብለዋል።

በሌላ በኩል ሩስያ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በዘፈቀደ ኃይል በመጠቀም የሰው ህይወት እያጠፋ ነው ያለቸው ርምጃ እንዲገታ ስትል ጠይቃለች።

የአፍሪካ ህብረት በበኩሉ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ መቆጠብን እንዳያሳይ አሳስቧል። የህብረቱ መሪዎች ኮሚቴ ዛሬ ዕሁድ ከሊቢያው መሪ ሞማር ጋዳፊ ጋር ለመነጋገር ወደትሪፖሊ ሊጉዋዝ የነበረው ዕቅድ መሰረዙን ለመረዳት ተችሏል።

XS
SM
MD
LG