በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኮምፒዩተር ንቃት ለገጠሬ ሕፃናት


የኮምፒዩተር ንቃት ለገጠሬ ሕፃናት
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:18 0:00

ዲጂታል ቴክኖሎጂው፣ የአንድ ዘመን ትውልዶች በአእምሮ የሚለያዩበት ሽብልቅ እንዳይኾን ያሳሰባት ኬንያዊት፣ ከዩናይትድ ስቴትስ ትምህርቷን አጠናቅቃ እንደተመለሰች፣ የኮምፒዩተር ተምህሮን ከገጠር መንደሯ ሕፃናት ጀምራለች፡፡

ይህ ዲጂታላዊ ሽብልቅ፣ በትምህርቱ ዘርፍ ከተደቀኑት ግዙፍ ፈተናዎች አንዱ እንደኾነ፣የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጥናት ያሳያል፡፡ እንደ ጥናቱ፥ ከሰሃራ ግርጌ ባሉት የአፍሪቃ ሀገራት፣ 82 በመቶ ተማሪዎች የበይነ መረብ አገልግሎት የማያገኙባቸው ሲኾኑ፣ ከተማሪዎቻቸው 90 በመቶ የሚኾኑቱ ደግሞ፣ ኮምፒዩተር በሌለበት ቤታቸው ይኖራሉ፡፡

“ቴክሊት አፍሪካ” የተሰኘው የበጎ አድራጎት ቡድን፣ በኬንያ፣ በርካታ የኮምፒዩተር ቤተ ሙከራዎችን በመገንባት፣ በትውልድ መካከል የተሰነቀረውን ዲጂታላዊ ቅርቃር የመለወጥ ውጥን አለው።

ጁማ ማጂያንጋ ከሞጎቲዮ ኬንያ ያጠናቀረው ዘገባ አሉላ ከበደ ወደ አማርኛ መልሶታል።

XS
SM
MD
LG