አፍሪካ ውስጥ ካሉት የስደተኛ ካምፖች ሁሉ ትልቁ የሆነው የኬንያው ዳዳብ የስደተኞች ካምፕ ሊስፋፋ ነው። የኬንያ መንግሥት በስደተኞች ብዛት የተጨናነቀው ካምፕ እንዲስፋፋ ተጨማሪ መሬት መስጠቱ ታውቋል።
የኬንያውን የስደተኛ ካምፕ ለማስፋፋት የተወሰነው በሺሆች የተቆጠሩ ሶማሊያውያን ከምንጊዜውም በላይ የከፋውን ድርቅ እና ረሃብ በመሸሽ ወደካምፑ እየጎረፉ ባሉበት ወቅት ነው።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ዘገባ ያገኛሉ።