የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በሀገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል አምስት ሚሊዮን ሰዎችን ባጠቃው ከፍተኛ ድርቅ ምክንያት የብሄራዊ አደጋ ዐዋጅ እንዲያውጁ የሚደረግባቸው ጫና እያየለ ነው።
ዝናብ ለስድስተኛ ተከታታይ ወቅት አለመጣሉ በቀጠናው ያለውን የረሃብ አደጋ እያባባሰው ሲሆን ኬንያ የሚገኘው ዘጋቢያችን አህመድ ሁሴን ከዋጂር አውራጃ እንደዘገበው፣ ከግማሽ በላይ የሚሆነው ሕዝብ ለከፍተኛ የምግብ እጥረት ተጋልጧል።
ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡