በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተመድ ያቋቋመው መርማሪ ኮሚሽን ውል እንዲቋረጥ ኢትዮጵያ ሐሳብ አቀረበች


ተመድ ያቋቋመው መርማሪ ኮሚሽን ውል እንዲቋረጥ ኢትዮጵያ ሐሳብ አቀረበች
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:55 0:00

በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን እንዲመረምር የተቋቋመው ዓለም አቀፍ የባለሞያዎች ኮሚሽን የሥራ ውል እንዲያቋርጥ የሚጠይቅ የውሳኔ ሃሳብ ማዘጋጀቷን ኢትዮጵያ አስታወቀች፡፡

የውሳኔ ሃሳቡን መዘጋጀት ዛሬ በተጀመረው የአፍሪካ ሕብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ንግግር ሲያደርጉ የገለጹት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የውሳኔ ሃሳቡ በቅርቡ ለሚካሔደው የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት እንደሚቀርብም ተናግረዋል፡፡

“በአፍሪካ ሕብረት መሪነት የተደረሰው የሰላም ሥምምነት ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ ማምጣት የሚለውን መርሃ ያንጸባረቀ ነው” ያሉት አቶ ደመቀ ለዚህም ምስጋና አቅርበዋለ፡፡

የሕብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ በበኩላቸው፣ ሕብረቱ ያለፈውን ዓመት በአህጉሪቱ ሠላምን በማውረድ ጉዳይ ተጠምዶ መቆየቱን ገልጸዋል፡፡

/ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

XS
SM
MD
LG