በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በትግራይ የሕክምና አገልግሎት መስጠት ፈታኝ ሆኗል


በትግራይ የሕክምና አገልግሎት መስጠት ፈታኝ ሆኗል
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:12 0:00

በትግራይ ክልል የህክምና አገልግሎት መስጠት እጅግ ፈታኝ ሆኖ መቀጠሉን ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ አስታወቀ።

የህክምና አገልግሎቱን ፈታኝ ያደረገው፣ በግጭቱ ወቅት ብዙ የጤና ተቋማት መውደም እና የአቅርቦት እጥረት መሆኑን ኮሚቴው ገልጿል።

የአምቡላንስ ችግርን ጨምሮ በሎጅስቲክስ አቅርቦት እጥረት ምክንያት የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበርም በመላው ትግራይ አገልግሎቱን በተሟላ መልኩ መጀመር እንዳልቻለ በክልሉ የማኅበሩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ብርሃኑ መኮንን ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የኮምዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ መስፍን ደረጀ በበኩላቸው ለችግሩ ምላሽ ለመስጠት ጥናት እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

ከችግሩ ውስብስብነት አንጻር ለጋሽ ድርጅቶች ድጋፋቸውን ሊያሳድጉ እንደሚገባ የገለጹት ደግሞ የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ፣ የምስራቅ አፍሪካ ቃል አቀባይ አሊዮና ሲኔንኮ ናቸው፡፡

XS
SM
MD
LG