በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰብዓዊ መብቶች ቀውስ የተመዘገበት ዓመት


የሰብዓዊ መብቶች ቀውስ የተመዘገበት ዓመት
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:34 0:00

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋጅ ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ዋች ያለፈው የአውሮፓውያን 2022 ዓ.ም በገመገመበት ዓመታዊ ሪፖርቱ “የሰብዓዊ መብቶች ቀውስ የተመዘገበት ዓመት” ብሎታል። ኢትዮጵያን በተመለከተ በወጣው የሪፖርቱ ክፍል ላይ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና ታጣቂ ቡድኖች በሌሎቹም የኢትዮጵያ ክልሎች በተለይም በኦሮሚያ ክልል ከባድ የመብት ረገጣዎች መፈፀማቸውን ገልጿል፡፡

የሂዩማን ራይትስ ዋች ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቲራና ሀሰን ኢትዮጵያን በተመለከተ በሰጡት አስተያየት “ለምሳሌ በትግራይ ክልል ለተፈፀሙ ዘግናኝ ወንጀሎች ተጠያቂነት እንዲኖር ማረጋገጥ የሰላም ስምምነቱ እውን እንዲሆን ወሳኝ ነው” ብለዋል።

ዓመቱ የመብት ጥሰት በስፋት የታየበት ቢሆንም በአዎንታዊ መልኩ ደግሞ ለሰብዓዊ መብት መከበር ቆመው የሚከራከሩ ተሟጋቾች የታዩበት ዓመትም እንደነበርም ሪፖርቱ አውስቷል፡፡ ሩስያ ዩክሬን ላይ ወረራ መክፈቷን ተከትሎ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ክትትል ለመዘርጋት በተደረገው ጥረት ፈጥኖ በመንቀሳቀሱ ሊመሰገን ይገባል ብሏል፡፡

XS
SM
MD
LG