በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የብሔራዊ ምክክሩ አጀንዳዎች ከኅብረተሰቡ የሚቀርቡቱ ብቻ ይኾናሉ - ኮሚሽነሩ - የሲዳማ ክልል ለብሔራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታወቀ


የብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን የሚያመካክርባቸው አጀንዳዎች፣ ከኅብረተሰቡ የሚቀርቡ እንደኾኑ ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርኣያ አስታወቁ። ከመንግሥት ወይም ከምሁራን ከላይ ወደ ታች የሚወርዱ ጉዳዮች፣ የኮሚሽኑ የምክክር አጀንዳዎች እንደማይኾኑ ኮሚሽነሩ አስታውቀዋል፡፡

ፕሮፌሰር መስፍን ይህን ያስታወቁት፣ ዛሬ በሐዋሳ ከተማ ከሲዳማ ክልል ፕሬዝዳንት ከአቶ ደስታ ሌዳሞ እና ከካቢኔያቸው ጋራ በጽ/ቤታቸው በመከሩበት ወቅት ነው፡፡ የሲዳማ ክልል ለኮሚሽኑ የሚያስፈልገውን የባለሞያ እና ሌሎች ድጋፎችን እንደሚያደርግ፣ ፕሬዚዳንቱ አቶ ደስታ ለኮሚሽነሩ አረጋግጠዋል።

ከዚህ ቀደም ለአሜሪካ ድምጽ አስተያየታቸውን የሰጡት የኦፌኮ፣ የአረና እና የኢዜማ አመራሮች፣ የኮሚሽኑ አባላት የተመረጡበት አካሔድ አካታች እንዳልሆነ እና አሁን በተያዘው መንገድ ውጤታማ መሆን ይቻላል ብለው እንደማያምኑ መግለፃቸው አይዘነጋም፡፡

በሌላ በኩል የኮሚሽኑ ተግባር በተለያዩ ልዩነቶች ዙሪያ ሁሉንም ኢትዮጵያውያን የሚያካትት ውይይት ለማድረግ እና ተግባቦት ለመፍጠር የሚያስችሉ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ብቻ መሆኑንም ከዚህ ቀደም የገለጹት ፕሮፌሰር መስፍን፣ በሂደቱ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ጨምሮ ፍላጎት ያላቸውን አካላት ሁሉ እንደሚያሳትፍም መናገራቸው አይዘነጋም።

የሐዋሳው ዘጋቢያችን ዮናታን ዘብዴዎስ ተጨማሪ ዘገባ ልኳል።

XS
SM
MD
LG