በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ግሪክ የሰጠሙ ስደተኞችን የማዳን ጥረቷን ቀጥላለች


ግሪክ የሰጠሙ ስደተኞችን የማዳን ጥረቷን ቀጥላለች
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:10 0:00

ስደተኞችን ጭኖ ይጓዝ የነበረ ጀልባ፣ ትላንት ረቡዕ፣ በግሪክ የባሕር ዳርቻ አቅራቢያ ተገልብጦ፣ በርካቶች መሞታቸውን ተከትሎ፣ ግሪክ፥ የሦስት ቀን ብሔራዊ ኀዘን ዐውጃለች።

በቅርብ ዓመታት ውስጥ፣ በግሪክ ከደረሱት አስከፊ አደጋዎች አንዱ እንደኾነ በተገለጸው በዚኽ የጀልባ መገልበጥ አደጋ፣ በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች መሞታቸው ቢረጋገጥም፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ግን፣ እስከ አሁን ያሉበት ባለመታወቁ፣ የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል፣ የግሪክ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

በጀልባው ተሳፍረው ከነበሩት አብዛኞቹ፥ ከግብፅ፣ ሶሪያ እና ፓኪስታን የመጡ እንደኾኑ ተነግሯል።የግሪክ ፕሬዚዳንት ካትሪና ሳኬላሮፑሉ፣ ከአደጋው ተርፈው፣ ካላማታ በተሰኘች የግሪክ ከተማ ወደሚገኝ መጠለያ የተወሰዱትን ስደተኞች ሲጎበኙ፣ የከተማዋ ከንቲባ ታናሲስ ቫሲሎፖለስ፣ ስደተኞቹን ለመርዳት የተለያዩ አገልግሎቶች እየቀረቡላቸው እንደሚገኝ ገልጸዋል።

“ለሁሉም ክብካቤ እያደረግን ነው። መጠለያ፣ መጸዳጃ፣ መታጠቢያ እና ሌላም የሚያስፈልጋቸውን አዘጋጅተናል። ሌሊቱን በዚኽ ሲያሳልፉ የሚበሉት እና ለነገ ቁርስ፣ ምሳ እና ራት የሚኾን ምግብም መጥቷል ነው፤” ያሉት ቫሊሎፖለስ።

ተብሮክ ከተሰኘ የሊቢያ ከተማ ተነሥቶ፣ ወደ ጣሊያን ሲያቀና እንደነበር በተገለጸው ጀልባ፣ ወደ 750 የሚደርሱ ሰዎች ተሳፍረው እንደነበር ይታመናል፤ ሲል፣ አላርም ፎን የተሰኘ የአደጋ ጊዜ በጎ አድራጎት ተቋም ሲያስታውቅ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ተቋም ደግሞ፣ የተሳፋሪዎቹ ቁጥር 400 እንደኾነ ገምቷል።

ግሪክ፣ ከመካከለኛው ምሥራቅ፣ እስያ እና አፍሪካ እየተነሡ ወደ አውሮፓ ኅብረት ለሚጓዙ ስደተኞች፣ ዋና መተላለፊያ መንገድ ስትኾን፣ በዚኽ ዓመት ብቻ፣ 72 ሺሕ የሚጠጉ

ስደተኞች እና ፍልሰተኞች፣ በአውሮፓ ግምባር ቀደም መዳረሻ ወደኾኑት ጣሊያን፣ ስፔን፣ ግሪክ፣ ማልታ እና ቆጵሮስ መግባታቸውን፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መረጃ ያመለክታል።

XS
SM
MD
LG