በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ “ብሪክስ”ን ለመቀላቀል ጥያቄ አቀረበች


ኢትዮጵያ “ብሪክስ”ን ለመቀላቀል ጥያቄ አቀረበች
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:34 0:00

ኢትዮጵያ፣ በምኅጻረ ቃሉ “ብሪክስ” በመባል የሚታወቀውን፣ የአምስት ፈጣን አዳጊ ሀገራት ጥምረት ለመቀላቀል ጥያቄ እንዳቀረበች፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ገለጹ።

በጉዳዩ ላይ፣ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጡ፣ የምጣኔ ሀብት ጉዳዮች ተመራማሪ እና ተንታኝ ዶር. ቆስጠንጢኖስ በርሄ፣ የብሪክስ አባል መሆን፣ ከምጣኔ ሀብት አንጻር ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸው፣ ፖለቲካዊ ተጽእኖ ግን ማስከተሉ እንደማይቀር አስተያየት ሰጥተዋል።

በዚህ ሒደት ኢትዮጵያ፣ በተለይ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋራ ያላት ግንኙነት እንዳይጎዳ፣ ጠንካራ የዲፕሎማሲ ሥራ እንደሚጠብቃትም ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ፣ የድርጅቱ አባል የመሆን ጥያቄዋ ተቀባይነት ከአገኘ፣ ከአባልነት ባለፈ ተጠቃሚ ለመሆን፣ በርካታ ማሻሻያዎችን ማድረግ እንደሚኖርባት አብራርተዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም፣ የኢትዮጵያ መንግሥት፣ የሰብአዊ ርዳታ አቅርቦቱን መቀጠል በሚችልበት አሠራር ላይ፣ ከለጋሽ ድርጅቶች ጋራ ንግግር እያደረገ እንደሚገኝና ሥርጭቱን በቅርቡ ሊጀመር እንደሚችል ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል የአገሪቱ ባለሥልጣናት፥ ርዳታ ለተገቢው ሰዎች እንደሚደርስ ካረጋገጡ፣ የዩናይትድ ስቴትስ የዓለምአቀፍ ልማት ኤጀንሲ /ዩኤስኤአይዲ/ አቋርጦት የነበረውን የምግብ ርዳታ በተቻለ ፍጥነት ዳግም በመቀጠል ላይ ማተኮር እንደሚሻ ገልጿል።

XS
SM
MD
LG