በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዑምራኩባ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ የእሳት አደጋ ጉዳት አደረሰ


በዑምራኩባ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ የእሳት አደጋ ጉዳት አደረሰ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:37 0:00

በሱዳን ዑምራኩባ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ ውስጥ፣ ትላንት ሌሊት ዐሥር ሰዓት ላይ በአጋጠመ የእሳት አደጋ ጉዳት መድረሱን፣ በዚያው በሱዳን ቱንያድባ በተባለ ቦታ እንደሚገኝ በስልክ የነገረን፣ ዮናስ ደባልቀው የተባለ አንድ ኢትዮጵያ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጿል።

የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ከሁለት ዓመት በፊት ሲቀሰቀስ፣ ከትግራይ ወደ ሱዳን የተሰደዱ ኢትዮጵያውያን በሚገኙበት በዚኽ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ የተነሣው እሳት መነሻው ምን እንደኾነ፣ ከጥርጣሬ ያለፈ የታወቀ ነገር አለመኖሩን ዮናስ ጨምሮ ገልጿል።

በዚኹ የዑምራኩባ መጠለያ ውስጥ፣ የእሳት ቃጠሎ አደጋ ሲያጋጥም የአሁኑ ለሦስተኛ ጊዜ ነው።

ከዚኽ ቀደም የእሳት አደጋ ሲያጋጥም፣ ስደተኞቹ ተረባርበው ማጥፋታቸውን ያስታወሰው ዮናስ፣ በአኹን አደጋም፣ በሱዳኑ ውጊያ ምክንያት አንድም የሚረዳ አካል በአካባቢው ባለመኖሩ፣ ስደተኞቹ በመተባበር ቃጠሎውን ማጥፋታቸውን ተናግሯል።

ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG