በሦርያና ቱርክ የደረሰውን ርዕደ-መሬት ተከትሎ የአደጋ ሰራተኞች አሁንም ፍርስራሹ ውስጥ በሕይወት የተቀበሩ ሰዎችን ለማዳን ጥረታቸውን በቀጠሉበት በዚህ ወቅት፣ የውሮፓ ኅብረትና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለአደጋው ሰለባዎች ያላቸውን ድጋፍ በመግለጽ ላይ ናቸው።
በሁለቱ አገሮች በድምር 22 ሺህ የሚደርስ ሕይወት የቀጠፈው አደጋ ከሃያ አምስት ዓመት ወዲህ ዓለም ያጋጠማት አስከፊ አደጋ ተደርጎ ተመዝግቧል።