በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ህወሓት ከሽብርተኝነት ዝርዝር እንዲነሳ ዛሬ ውሳኔ አስተላለፈ


የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ህወሓት ከሽብርተኝነት ዝርዝር እንዲነሳ ዛሬ ውሳኔ አስተላለፈ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:38 0:00

ህወሓት ከሽብርተኝነት እንዲነሳ በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ፣ ከምክር ቤት አባላት “ጠንካራ የተቃውሞ አስተያየቶች” መሰንዘራቸውን የአሜሪካ ድምጽ ከውስጥ ምንጮች ለመረዳት ችሏል፡፡

“ህወሓት ቀድሞውንም በአሸባሪነት መፈረጅ አልነበረበትም” ያሉት የፓርቲው የአደረጃጅት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተወልደ ገብረፃድቃን፤ የዛሬው ውሳኔ ለትግራይ ክልል ህዝብ እና ለፓርቲው በነጻነት መንቀሳቀስ ፋይዳ አለው” ሲሉ ውሳኔውን አድንቀዋል፡፡

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የፓርላማ አባል ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ በበኩላቸው ህወሃት በሽብርተኝነት መፈረጅ ከነበረበት ጊዜ ዘግይቶ መፈረጁን ጠቅሰው፣ “ዛሬ የተላለፈው ውሳኔም ወቅቱን ያልጠበቀ ነው” ሲሉ አጥብቀው ተቃውመዋል፡፡

የፌዴራል መንግሥት በአንጻሩ: ውሳኔው ዘላቂ ሠላም ለማምጣት አስፈላጊ ነው ብሏል፡፡

ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG