የኢትዮጵያ መንግሥት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ የኢትዮጵያ ክፍሎች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ለረሃብ አደጋ ያጋለጠውን ድርቅ በይፋ አለማረጋገጡ ዓለም አቀፍ እርዳታዎች እንዳይፋጠኑ እና የድርቅ ተጎጂዎች ተገቢውን እርዳታ በወቅቱ እንዳያገኙ እያደረገ ነው፤ ሲሉ የእርዳታ ተቋማትና ተንታኞች ተናገሩ።
ለሦስት ዓመታት ዝናብ ባለመዝነቡ ድርቁ ባጠቃቸው አካባቢዎች 12 ሚሊዮን ሰዎች ለምግብ እጥረት፣ ለውሃ ጥም እና ለበሽታ የተዳረጉ ሲሆን ከ 4.5 ሚሊየን በላይ ከብቶችም ሞተዋል። ዘገባውን ከተያያዘው ፍይል ይከታተሉ።