የኢትዮጵያ ቡና ማኅበር በሀገር ውስጥ ገበያ ቡናን በውጭ ምንዛሪ መገበያየት ሊጀመር እንደሆነ አስታወቀ፡፡ ማሕበሩ የተመሰረተበትን 50ኛ አመት በማስመልከት በሰጠው መግለጫ፣ በሀገር ውስጥ ገበያ ቡናን በውጭ ምንዛሪ መሸጥ ጠቀሜታው የጎላ ነው ብሏል፡፡
የማኅበሩ ቦርድ ፕሬዚዳንት አቶ ደሳለኝ ጀና እና የቦርድ አባላቱ በጋራ በሰጡት መግለጫ፣ በቡና ግብይት ላይ የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ የተለያዩ እርምጃዎች መወሰዳቸውን ገልፀዋል፡፡
በሀገር ውስጥ የቡና ዋጋ እየናረ መምጣቱን የተናገሩት አባላቱ፣ ባለፉት አምስት አመታት ብቻ ዋጋው ከእጥፍ በላይ መጨመሩን አመልክተዋል፡፡ ይህም የአቅርቦት እጥረት የፈጠረው ችግር እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ።