በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሀገር ውስጥ የስንዴ ገበያ ለችግር መጋለጡን ተጠቃሚዎች እየተናገሩ ነው


የሀገር ውስጥ የስንዴ ገበያ ለችግር መጋለጡን ተጠቃሚዎች እየተናገሩ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:39 0:00

ኢትዮጵያ ለውጭ ገበያ ስንዴ እንደምታቀርብ በገለጸችበት በአሁኑ ወቅት የሀገር ውስጥ የስንዴ ገበያ ለችግር መዳረጉን ተጠቃሚዎች ይገልፃሉ። ሀገሪቱ ፍጆታዋን ሸፍና 32 ሚልዮን ኩንታል ያህል ስንዴ ለውጭ ገበያ የማቅረብ አቅም እንዳላት መንግሥት ከጥቂት ቀናት በፊት መግለጹ ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጂ አንዳንድ የዱቄት ፋብሪካዎች በግብዓት እጥረት ምክንያት ሥራ ማቆማቸውን የዱቄት አምራቾች ማኅበር ለአሜሪካ ድምፅ አስታውቋል፡፡ ከስንዴ ወደ ውጭ መላክ ጋራ በተያያዘ አስተያየታቸውን የሰጡን የምጣኔ ኃብት ባለሙያዎች በበኩላቸው፣ እጥረት እያለም ቢሆን ምርቶችን ለውጭ ገበያ ማቅረብ ከውጭ ምንዛሪ ፍላጎት እና ከፖለቲካ ግብ ጋር በተያያዘ መልኩ የተለመደ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ሆኖም ዋናው ጉዳይ በዚህ ሁኔታ የሚገኘው የውጭ ምንዛሪ ለምን አገልግሎት ይውላል የሚለው እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG