በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“የአሜሪካ የሰብአዊ መብቶች ሪፖርት ከጣምራ ቡድኑ ሪፖርት ጋራ በአመዛኙ ተመሳሳይ ነው” - ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ


የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት፣ ኢትዮጵያን በሚመለከት በቅርቡ ያወጣው የሰብአዊ መብት ሪፖርት፣ ከጣምራ ቡድኑ ሪፖርት ጋራ በአመዛኙ ተመሳሳይ እንደ ኾነ የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ ገለጹ፡፡

የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ፣ ሰሞኑን በአወጣው ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሪፖርት፣ በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት የተሳተፉ ኹሉም ኃይሎች፤ የጦር ወንጀል መፈጸማቸውን፣ ከህወሓት በስተቀር ያሉት ኃይሎች ደግሞ በሰብአዊነት ላይ ወንጀል መፈጸማቸውን አስታውቋል፡፡ ይኹን እንጂ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ሪፖርቱን እንደማይቀበለው ገልጿል፡፡

ስለዚኹ ጉዳይ፣ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጡት የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ሪፖርት፣ ከዚኽ ቀደም ይፋ ከኾነው የጣምራ ቡድኑ ሪፖርት ጋራ በአመዛኙ ተመሳሳይ መኾኑን ተናግረዋል፡፡

በጣምራ ቡድኑ ምክረ ሐሳብ ላይ በመመሥረት ስለተጀመረው የሽግግር ፍትሕ ሒደት፣ ከዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልኡክ ማይክ ሐመር ጋራ መወያየታቸውንም ዳንኤል ገልጸዋል፡፡ ዋና ኮሚሽነሩ አያይዘውም፣ ለተመድ የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ማብራሪያ መስጠታቸውን ጠቅሰው፣ ምክር ቤቱ ድጋፉን እንደ ቸረ አስታውቀዋል፡፡

ሙሉዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

XS
SM
MD
LG