በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቱሪዝም ዘርፉ ላይ የተጣለው የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲነሳ ተጠየቀ


በቱሪዝም ዘርፉ ላይ የተጣለው የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲነሳ ተጠየቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:20 0:00

የኢትዮጵያ ቱሪዝም አስጎብኝዎች ማኅበር በዘርፉ ላይ የተጣለው የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲነሳ ጥሪ አቀረበ። የቱሪዝም ዘርፉ በተለያዩ ችግሮች ተፅዕኖ ስለደረሰበት፣ መንግሥት ተጨማሪ እሴት ታክስን በማንሳት ዘርፉ እንዲያንሰራራ ማገዝ አለበት በማለት የኢትዮጵያ አስጎብኝዎች ማህበር ፕሬዚዳንት ወይዘሮ አንድነት ዘለቀ ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል፡፡

ማኅበሩ ይህን ጥያቄ በተለያዩ መድረኮች ለመንግሥት አካላት ቢያቀርብም፣ ምላሽ እንዳልተገኘና በተሻሻለው ረቂቅ የተጨማሪ እሴት ታክስ ዐዋጅ ላይም ለውጥ እንደሌለ ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት በበኩሉ የቱሪዝም ዘርፉ ለሀገሪቱ የውጭ ምንዛሪን የሚያስገኝ በመሆኑ፣ በወጪ ንግድ ላይ ለተሰማሩ ባለሃብቶች የሚደረገው ማበረታቻ ያህል ሊደረግለት ይገባል ብሏል፡፡

በምክር ቤቱ፣ ከፍተኛ የስራ ኃላፊ አቶ ዮሃንስ ወልደገብርኤል ምክር ቤቱ የአስጎብኝዎች ማኅበርን ጥያቄ ለመንግሥት እንዳቀረበ ተናግረዋል፡፡ ስለዚህ ጉዳይ ከቱሪዝም ሚኒስቴር አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ፡፡

XS
SM
MD
LG