ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ ከፍተኛ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት በደቡብ አፍሪካ በተፈረመው የሠላም ሥምምነት ሂደት እና አተገባበር ዙሪያ ዛሬ ውይይት አድርገዋል።
ውይይቱ መደረጉን የገለጹት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፣ የመልሶ ማቋቋም፣ የመልሶ ግንባታ፣ የህዝባዊ እና የዲፕሎማሲ ሥራዎችን ለማፋጠን የተለያዩ ቡድኖች ተቋቁመዋል ብለዋል፡፡
የህወሓት ባለሥልጣናት ግን ከሥምምነቱ በኋላ እስካሁን በይፋ የሰጡት አስተያየት የለም፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት የሠላም ሥምምነቱን ዝርዝር ሰነድም ዛሬ ይፋ አድርጓል፡፡
በተያያዘ ትናንት በአርባምንጭ ከተማ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ኢትዮጵያዊያን ለትግራይ ክልል መልሶ ግምባታ በጋራ እንዲሰሩ ጠይቀዋል፡፡
ሥምምነቱ አሁንም ከተለያዩ አካላት አድናቆት እየተቸረው ነው፡፡