ለሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት መፍትሄ ለማምጣት የምታደርገውን ጥረት መቀጠሏን ዩናይትድ ስቴትስ ገለፃች።
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ “ግጭቱን ለማስቆም የአፍሪካ ኅብረት የሚያደርገው ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ውጤታማ እንዲሆን፣ የምንችለውን ሁሉ እያደረግን ነው” ብለዋል፡፡
ይሁን እንጂ በሁለቱ ተፋላሚ ወገኖች መካከል መተማመን አለመኖሩ ለሰሜኑ ጦርነት ሰላማዊ መፍትሔ ለማምጣት ከፍተኛ እንቅፋት መሆኑን የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ማይክ ሀመር መግለጻቸው ይታወሳል፡፡
ኔድ ፕራይስ ትናንት መግለጫ ሲሰጡ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ለህወሓት እንደምትወግን በመግለጽ ለተነሳላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ “እኛ የምንደግፈው የሰላምን ጉዳይ ነው” ብለዋል፡፡