በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የታለመ የነዳጅ ድጎማ አፈጻጸም እና የአሽከርካሪዎች ቅሬታ


የታለመ የነዳጅ ድጎማ አፈጻጸም እና የአሽከርካሪዎች ቅሬታ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:55 0:00

በአሠራር ችግር ምክንያት መንግሥት ከሰጠን የነዳጅ ድጎማ ዕድል እየተጠቀምን አይደለም፤ ሲሉ አሽከርካሪዎች ቅሬታቸውን አሰሙ፡፡

የታለመ የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚ የኾኑ አሽከርካሪዎች፣ በአፈጻጸሙ ላይ እየታዩ ባሉት ችግሮች ምክንያት፣ “መንግሥት በሰጠን ዕድል እየተጠቀምን አይደለንም፤” አሉ፡፡

የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በበኩሉ፣ “የታለመ የነዳጅ ድጎማ አሠራርን ለመተግበር ሥራ ላይ የዋለው ቴክኖሎጂ ውጤታማነቱ የተረጋገጠ ቢኾንም፣ በሒደት የሚታዩትን ችግሮች ለማስተካከል፣ አተገባበሩን የሚቆጣጠር ግብረ ኀይል አቋቁመን እየሠራን ነው፤” ብሏል፡፡

ስለ ጉዳዩ ለቪኦኤ ማብራሪያ የሰጡት የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሐሰን መሐመድ፣ የነዳጅ ድጎማው መቀነስ የኑሮ ውድነትን ያባብሳል፤ የሚለው አስተያየት፣ በማስረጃ ያልተደገፈ ነው፤ ብለውታል፡፡ መንግሥት የነዳጅ ድጎማን በሒደት እየቀነሰ ቢኾንም፣ አሁንም የልዩ ልዩ ሸቀጦችን ወጪ እየደጎመ የኑሮ ውድነቱን ለማረጋጋት እየሠራ እንደኾነ ገልጸዋል፡፡

/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

XS
SM
MD
LG