በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቡርሃን ልዩ መልዕክተኛ በዐዲስ አበባ


የቡርሃን ልዩ መልዕክተኛ በዐዲስ አበባ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:03 0:00

የሱዳን ጦር አዛዥ አብዱል ፋታህ አል ቡርሃን ልዑክ፤ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ እና ከአፍሪካ ኅብረት ሊቀ መንበር ጋር ተነጋገሩ።

"ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ቀድሞ መሣሪያውን ካስቀመጠ እኛም ውጊያውን በፍጥነት ለማቆም ዝግጁ ነን" ሲሉ ወደ ኢትዮጲያ የተጓዙት ልዩ መልዕክተኛው ዳፋ-አላህ ኤልሃጂ ተናገሩ።

ኤልሃጂ ትላናንት ሐሙስ አዲስ አበባ ላይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ፤ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር አቢይ አህመድ እና ከአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሐማት መወያየታቸውን ገልጸዋል።

"የሱዳን መንግሥት አመጹን በአጭር ጊዜ እንደሚያስቆም፣ የአካባቢያችን ሰላም እና መረጋጋት ጉዳይ በእጅጉ እንደምናስብበት አረጋግጬላቸዋለሁ" ያሉት ልዩ ልዑኩ "መሳሪያውን ለማስቀመጥ የሚፈልግ ኺሉ አሁንም ቢሆን ምህረት የማግኘት ዕድል አለው" ብለዋል።

በሮይተርስ እና በአሶሲየትድ ፕሬስ የተጠናቀሩትን ዘገባዎች ያድምጡ

XS
SM
MD
LG