የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን፣ ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በተጨማሪ ከሲቪል ማኅበራትና የሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ጋር በኢትዮጵያ ባለው ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ተወያይተዋል።
ውይይቱን በማስመልከት ለአሜሪካ ድምጽ ማብራሪያ የሰጡት የመብቶችና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) የፕሮግራም ኃላፊ መንግሥቱ አሰፋ፣ በውይይታቸው በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ያሉ ግጭቶች ስለሚፈቱበት ጉዳይ ማንሳታቸውን ገልጸዋል፡፡
በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት ተጠያቂነትን ማስፈንና የሽግግር ፍትህን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ብሊንከን መግለፃቸውንም አንስተዋል፡፡
የዩናይትድ ስቴትስና የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባዮች በሰጡት መግለጫም፣ የብሊንከን ጉብኝት በሁለቱ ሀገሮች መካከል ያለው ግንኙነት እየተሸሻለ መሆኑን እንደሚያሳይ አስታውቀዋል፡፡
ብሊንከን ዛሬ ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ጋር የተወያዩ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ቆይታቸውን አጠናቀው ወደ ኒጀር አቅንተዋል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።