በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቤት ማፍረሱ እና የግዳጅ ማፈናቀሉ ሕገ ወጥ እንደኾነ ኢሰመጉ ገለጸ


 የቤት ማፍረሱ እና የግዳጅ ማፈናቀሉ ሕገ ወጥ እንደኾነ ኢሰመጉ ገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:00 0:00

ከጥቅምት 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በዐዲስ አበባ፣ በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ አስተዳደር እና በአዳማ ከተሞች፣ የ111ሺሕ811 አባወራ እና እማወራ ቤቶች መፍረሳቸውን፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ አስታወቀ፡፡

የኢሰመጉ ምክትል ዋና ዲሬክተር አቶ ተስፋዬ ገመቹ፣ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ማብራሪያ፣ የቤት ማፍረስ እና አስገድዶ ማፈናቀል ርምጃ፣ ከሕግ አግባብ ውጭ የሚፈጸም እንደኾነ አስረድተዋል፡፡

የአሜሪካ ድምፅ፣ የኢሰመጉን ሪፖርት በተመለከተ ከልዩ ልዩ የመንግሥት አካላት፣ ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ጥረት ሊሳካ አልቻለም፡፡

ሆኖም፣ ትላንት ለሀገር ውስጥ ብዙኃን መገናኛ መግለጫ የሰጡት፣ የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ሓላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ፣ ቤቶችን የማፍረስ ርምጃው፣ ሕገ ወጥነትን ለመከላከል የሚደረግ መኾኑንና ይኸውም ከ600 በላይ ከተሞች ላይ እየተካሔደ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

ከሰብአዊ መብቶች ተቋማት በተጨማሪ፣ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችም፣ ርምጃውን ተቃውመው መግለጫ አውጥተዋል፡፡ ከነዚኽ መካከል የኾነው፣ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ(ኦፌኮ)፣ “ድርጊቱ ሕጋዊነትን ያልተከተለ፣ በተሳሳተ ፖሊሲ ላይ የተመሠረተ፣ ወቅታዊነትንም ያላገናዘበ ነው፤” ብሏል፡፡በሌላ በኩል፣ የቤት ማፍረሱ አሁንም መቀጠሉን ተጎጂዎች ገልጸዋል፡፡

XS
SM
MD
LG