በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢሰመኮ በኦሮሚያ ክልል ይፈፀማሉ ባላቸው የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ፖሊስን ተቸ


ኢሰመኮ በኦሮሚያ ክልል ይፈፀማሉ ባላቸው የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ፖሊስን ተቸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:11 0:00

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)፣ የኦሮሚያ ፖሊስ፥ በተጠርጣሪዎች ላይ የመብት ጥሰት እየፈጸመ ነው፤ ሲል ተቸ።

የኮሚሽኑ የጅማ ቅርንጫፍ ቢሮ ሓላፊ አቶ በዳሳ ለሜሳ፣ አሁንም በክልሉ የተለያዩ የፖሊስ ጣቢያዎች፣ የወንጀል ተጠርጣሪዎች ለፍርድ ሳይቀርቡ ለወራት እንደሚቆዩና በኢ-መደበኛ ቦታዎች ሳይቀር ተጠርጣሪዎች እንደሚታሰሩ፣ በክትትላችን ደርሰንበታል፤ ብለዋል።

ነዋሪዎች አሁንም፣ “በክልሉ የጸጥታ ነባራዊ ሁኔታ” በሚል ተጠርጥረው ታስረው የተፈቱና በእስር ላይ ያሉም እንዳሉ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል። የኦሮሚያ ክልል የፍትሕ እና ሰላም ክላስተር ቢሮ፣ በጉዳዩ ላይ ምላሽ ሰጥቷል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG