በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በምዕራብ ትግራይ “ዘር ማጽዳት ተፈጽሟል” ሲል ሂዩማን ራይትስ ዋች አስታወቀ


በምዕራብ ትግራይ “ዘር ማጽዳት ተፈጽሟል” ሲል ሂዩማን ራይትስ ዋች አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:07 0:00

በኢትዮጵያ መንግሥት እና በህወሓት መካከል፣ የፕሪቶርያው ስምምነት ከተደረገ ልክ በሰባተኛ ወሩ፣ በአዛጋቢው ወልቃይት እና ሑመራ አካባቢ፣ የዘር ማጽዳት እየተካሔደ ነው፤ ሲል፣ ሂዩማን ራይትስ ዋች፣ ዛሬ ባወጣው ሪፖርት አስታወቀ፡፡

ሂውማን ራይትስ ዋች፣ “የዐማራ ኃይሎች እና የአካባቢው ባለሥልጣናት፣ በጉልበት የትግራይ ተወላጆችን ማፈናቀላቸውን ቀጥለዋል፤” ያለ ሲኾን፣ የኢትዮጵያ መንግሥት፣ ይህን ተግባር በመፈጸም ላይ የሚገኙ የጸጥታ ኃይሎችን እንዲያግድ፣ እንዲመረመርና በአግባቡ እንዲቀጣ ሲል ጥሪ አቅርቧል፡፡

በተጨማሪም፣ በጉልበት ከቀዬአቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ወደ መኖሪያቸው እንዲመለሱ ዓለም አቀፍ ሕጎች ቢጠይቁም፣ አሁን ባለው ኹኔታ፣ የትግራይ ተወላጆች፥ በፈቃደኝነት፣ ደኅንነት ተሰምቷቸውና ክብራቸውን በጠበቀ መልኩ የሚመለሱበት ኹኔታ የለም፤ ብሏል፡፡

“ኅዳር ላይ የተደረገው የተኩስ አቁም፣ በምዕራብ ትግራይ ያለውን የዘር ማጽዳት ዘመቻ በምንም ምልኩ አላስቆመውም፤” ያሉት፣ የድርጅቱ የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል ዳይሬክተር ላቲሺያ ባደር፣ “የኢትዮጵያ መንግሥት፣ ተበዳዮች ፍትሕ እንዲያገኙ ቁርጠኛ ከኾነ፣ በምዕራብ ትግራይ በደል እየፈጸሙ ባሉ ባለሥልጣናት እና የጦር መሪዎች ላይ፣ ገለልተኛ ምርመራዎች የማድረጉን ሒደት መቃወሙን ማቆም አለበት፤” ሲሉ አሳስበዋል፡፡

በሪፖርቱ ላይ የተጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG