በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"የህወሓት ታጣቂዎች በዋግ ሕምራ ዞን በተፈናቃዮች መጠለያ ላይ 26 ንጹሃንን ገድለዋል” - የዞኑ አስተዳደር


"የህወሓት ታጣቂዎች በዋግ ሕምራ ዞን በተፈናቃዮች መጠለያ ላይ 26 ንጹሃንን ገድለዋል” - የዞኑ አስተዳደር
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:34 0:00

"የህወሓት ታጣቂዎች በዋግ ሕምራ ዞን ወለህ መጠለያ ጣቢያ በሚገኙ ተፈናቃዮች ላይ ጥቃት በመፈጸም 26 ንጹሃንን ገድለዋል" ሲል የዞኑ አስተዳደር አስታውቋል ።

የዞኑ አስተዳደር የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ከፍያለው ደበሽ ለአሜሪካ ድምጽ እንዳሉት በዚሁ ጥቃት የቆሰሉ ሌሎች ሰባት ሰዎች ደግሞ በሰቆጣ ከተማ በሚገኝ ሆስፒታል ሕክምና በመከታተል ላይ ናቸው።

ከህወሓት በኩል በዚህ ጥቃት ዙሪያ የተሰማ ቀጥተኛ ምላሽ ባይኖርም ቀደም ሲል የተሰነዘሩ መሰል ውንጀላዎችን ሲያስተባብል መቆየቱ ይታወሳል።

የህወሓት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ ሰሞኑን ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ ተዋጊዎቻቸው ሕዝብን ኢላማ እንደማያደርጉና የተማረኩ ታጣቂዎችን ሳይቀር በተገቢው መንገድ እንደሚይዙ ተናግረዋል።

XS
SM
MD
LG