በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጉጂ እና ቡርጂ ጉዳይ በሽማግሌዎች እንዳልተፈታ ነዋሪዎች ገለፁ


የጉጂ እና ቡርጂ ጉዳይ በሽማግሌዎች እንዳልተፈታ ነዋሪዎች ገለፁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:55 0:00

በደቡብ ክልል ቡርጂ ልዩ ወረዳ ሶየማ ከተማ ውስጥ ግንቦት 27/2014 ዓ.ም በምዕራብ ጉጂ ዞን ተወላጆች ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ የተፈጠረው አለመግባባት በሃገር ሽማግሌዎች መፍትሔ አለማግኘቱን ገለፁ።

በኦሮምያ ክልል የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች አንድ የቡርጂ ተወላጅ ገድለዋል መባሉን ተከትሎ በተጠቀሰው ቀን ዘጠኝ የጉጂ ተወላጆች ከተገደሉ በኋላ በአካባቢው የተፈጠረው ውጥረት እስካሁን አለመብረዱን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል ።

ምእራብ ጉጂ ዞን ሱሮ በርጉዳ ወረዳ ወሌና ቦኮሳ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አቶ ደንቦበ ቅርጫ፤ “የሰው ሕይወት በአካባቢው ከጠፋ ወዲህ የእርስ በእርስ ግንኝነቶች ተቋርጠዋል” ብለዋል።

ግብይት በመቋረጡም በሁለቱም በኩል ነዋሪዎች ለችግር መዳረጋቸውን ገልፀው፤ ከዚህ ቀደም በተገባላቸው ቃል መሰረት ችግሮቹ በሽምግልና እንዲፈቱ ጠይቀዋል። የቡርጂ ልዩ ወረዳ አስተዳዳሪ ጉዳዩን በቅርቡ እንደሚፈታ ተናግረዋል።

XS
SM
MD
LG