በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የግልገል በለስ ከተማ ነዋሪዎች ለመፈናቀል መዳረጋቸውን ገለፁ


የግልገል በለስ ከተማ ነዋሪዎች ለመፈናቀል መዳረጋቸውን ገለፁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:47 0:00

- ከተማ ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ መመለሱን የዞኑ አስተዳዳሪ ተናግረዋል

የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የግልገል በለስ ከተማ ነዋሪዎች ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ ከተማዋን ለቀው ወደ ፓዊ ቻግኒ እየተሰደዱ ያሉ ነዋሪዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ተናግረዋል::

ከተማዋን ለቀው ከሸሹት ግለሰብ መካከል አንዱ እንደተናገሩት ከመንግስት የፀጥታ አካላት ውጭ በከተማው ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ ሀይሎች መታየታቸው ለስጋታቸው ምክንያት መሆኑን ገልፀዋል ::

የመተከል ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶለሜሳ ዋወያ ግን በከተማው ተከስቶ የነበረው ግጭት ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ መመለሱን ገልፀው፤ “በእርቀ ሰላም ስም የገቡ ታጣቂዎች ካምፕ ውስጥ ነው ያሉት” በማለት ድርጊቱን አስተባብለዋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ባወጣው መግለጫ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ ግልገል በለስ ከተማ ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም በክልሉ ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ ቡድኖች ባደረሱት ጥቃት ምክንያት በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰዎች መገደላቸን፣ መቁሰላቸውን እና ለደህንነታቸው በመስጋት አካባቢውን ለቀው መውጣታቸውን ተናግረዋል።

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን በተደጋጋሚ እየተፈጸሙ ያሉ እና በክልሉ መንግስት ዘላቂ መፍትሄ ሊያገኙ ያልቻሉ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን በአስቸኳይ እንዲያስቆም ጉባኤው ለመንግስት ጥሪም አቅርቧል

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG