በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ተሽከርካሪዎች የተወሰዱባቸው ባለንብረቶች አቤቱታ


በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ተሽከርካሪዎች የተወሰዱባቸው ባለንብረቶች አቤቱታ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:41 0:00

- የተማረኩ እንጂ የተዘረፉ ተሽከርካሪዎች የሉም - ትግራይ ክልል

በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ተሽከርካሪዎቻቸው እንደተዘረፉባቸው የሚናገሩ ባለንብረቶች ችግር ላይ መሆናቸውን ገለፁ፡፡

“በጦርነቱ ምክንያት ቤተሰቦቻችንን የምናስተዳደርባቸው ተሸከርካሪዎቻችን በመዘረፋቸው ለከፋ ችግር ተጋልጠናል” ሲሉ በአማራ ክልል ኮምቦልቻና ቃሉ ወረዳ የሚኖሩ ቅሬታ አቅራቢዎች ገለጹ።

“ተሸከርካሪዎቻችን ትግራይ ውስጥ መኖራቸውን አረጋግጠናል” የሚሉት ከ50 የሚበልጡ ቅሬታ አቅራቢዎች መንግሥት የሰላም ሥምምነቱን ከተፈራራመ የተዘረፉ ንብረቶችንም ጉዳይ ትኩረት እንዲሰጠው ጠይቀዋል።

የትግራይ ክልል ትራንስፖርትና መገናኛ ቢሮ ደግሞ “የተማረኩ’’ ሲሉ የገለጿቸውን የግለሰብ ተሸከርካሪዎች ለባለንብረቶቹ መመለስ ፖሊሲው እንደሆነ ጠቅሶ ለዚህም ፌዴራል መንግሥቱና ክልሎች በጋራ መሥራት እንደሚገባቸው አመልክቷል።

በአንፃሩም ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ ጀምሮ ከትግራይም የተዘረፉ ከስድስት ሺህ በላይ ተሸከርካሪዎች እንዳሉ ቢሮው ገልፆ ለማስመለሱ ፌዴራል እገዛ እንዲያደርግ ጠይቋል።

ከ77 በላይ የግለሰብና የመንግሥት ተሸክርካሪዎች በጦርነቱ ተዘርፈዋል የሚለው የአማራ ክልል መልሶ ማቋቋምና ግንባታ ፈንድ ጽ/ቤት በበኩሉ የቅሬታ አቅራቢዎቹን ጥያቄ ለመመለስ የአቅም ውስንነት እንዳለበት ገልጾ የሚመለከታቸው ዓለም አቀፍና የአገር ውስጥ ተቋማት ጉዳዩን እንዲያውቁት ማድረጉን ጠቁሟል፡፡

/ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

XS
SM
MD
LG