በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በግጭት ምክንያት ከኦሮምያ ወደ አማራ ክልል የሚሰደዱ ተፈናቃዮች ቁጥር ማሻቀቡን ኦቻ ተናገረ


በግጭት ምክንያት ከኦሮምያ ወደ አማራ ክልል የሚሰደዱ ተፈናቃዮች ቁጥር ማሻቀቡን ኦቻ ተናገረ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:35 0:00

በግጭት ምክንያት ከኦሮምያ ክልል ወደ አማራ ክልል የሚሰደዱ ተፈናቃዮች ቁጥር ማሻቀቡን የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ፅ/ቤት (ዩኤን ኦቻ) አስታውቋል።

ጽ/ቤቱ የአካባቢውን ባለሥልጣናት እና የሰብዓዊ እርዳታ ሠራተኞችን ጠቅሶ ባወጣው ሪፖርት ከኦሮምያ ክልል የወለጋ ዞኖች የተሰደዱ በርካታ ተፈናቃዮች በተከታታይ ወደ አማራ ክልል የተለያዩ ዞኖች እየገቡ ነው ብሏል።

የአማራ ክልል አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን በበኩሉ በወለጋ ዞኖችና አጎራባች አካባቢዎች በሚፈጸም ጥቃት ምክንያት ባለፉት አራት ዓመታት በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች ወደ ወደተለያዩ የአማራ አካባቢዎች መሰደዳቸውን አመልክቷል።

ባሕር ዳር በሚገኘው የአማራ ክልል የአደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን በር ላይ ተሰብሰበው ያነጋገርናቸው ተፈናቃዮች ቀያቸውን ትተው የተሰደዱት ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራውና በኢትዮጵያ ፓርላማ ሸኔ በሚል በአሸባሪነት የተፈረጀው ቡድን በሚፈጽመው ግድያ ምክንያት ነው ብለዋል። ቡድኑ የቀረቡበትን መሰል ውንጀላዎች በተደጋጋሚ አስተባብሏል።

[ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ]

XS
SM
MD
LG