በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካ መሪዎች ሩሲያንና ዩክሬንን ለማሸማገል ሊጓዙ ነው


የአፍሪካ መሪዎች ሩሲያንና ዩክሬንን ለማሸማገል ሊጓዙ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:00 0:00

የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች፣ በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል የሚካሔደው ጦርነት ቆሞ ሰላም እንዲወርድ ለማሸማገል፣ በቀጣዮቹ ቀናት ወደ ሞስኮ እና ወደ ኪቭ ከተሞች ይጓዛሉ፡፡

የመሪዎቹን ልዑካን የምትመራው ደቡብ አፍሪካ ናት፡፡ደቡብ አፍሪካ ደግሞ፣ ጦርነቱን በሚመለከት፣ በአደባባይ ገለልተኛ አቋም እንደምትከተል ብትናገርም፣ ሩሲያን ትደግፋለች በሚል ትከሠሣለች፡፡

ለጦርነቱ መፍትሔ ለመፈለግ፣ ከአሁን ቀደም የሽምግልና ጥረት ያደረጉ ሌሎች አካላት እንዳልሠመረላቸው ይታወቃል፡፡ኬት ባርትሌት ከጆሀንስበርግ ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG