በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ዓዲግራት ከተማ ገባ


የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ዓዲግራት ከተማ ገባ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:23 0:00

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ማክሰኞ ጥር 9፤ 2015 ዓ.ም ዓዲግራት ከተማ መግባቱን እና ከጦርነቱ በፊት ይጠቀምበት የነበረው ወታደራዊ ካምፕ መቀመጡን የከተማዋ ከተማ ከንቲባ አቶ ላዕከ ተስፋ መስቀል ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ።

“በሥምምነቱ መሰረት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ወደ አዲግራት ገብተዋል” ያሉት አቶ ላዕከ “የከተማው አስተዳደርም በቦታው ነው ያለው። ፖሊስና የሚሊሺያ አካላትም በሕገ መንግሥቱ መሰረት ሥራቸውን እያከናወኑ ነው” ብለዋል። የኤርትራ ሰራዊት አባላት በከተማዋ ቅርብ ርቀት ላይ እንደሚገኙ የገለፁት ከንቲባው የሰራዊቱ አለመውጣት ኅብረተሰቡ ላይ ሥጋት መፍጠሩን ገልፀዋል።

ቪኦኤ ያነጋገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች በበኩላቸው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት የኢትዮጵያን ባንዲራ ይዘው በሰልፍ በሰላም ሲገቡ ማየታቸውንና በዚህም ምንም ስጋት እንደሌለባቸው ተናግረዋል። ነገር ግን የኤርትራ ሰራዊት በከተማዋ ቅርብ ርቀት ላይ መኖሩ በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያሰጋቸው ተናግረዋል።

ከደረሰባቸው ግፍ አኳያ የኤርትራ ሰራዊት ስም ሲነሳ ሕፃናቶች ሳይቀር እንደሚደነግጡ የገለፁት የከተማዋ ነዋሪ ከዚህ በኋላ ሕዝቡ ያለስጋት በሰላም እንዲኖር “ወደመጡበት ይመለሱ” ብለዋል።

የኤርትራ መንግሥት በተደጋጋሚ እየተወነጀለ በሚገኝበት ከትግራይ ክልል ሙሉ ለሙሉ ለቆ የመውጣት ጉዳይ እስካሁን ያለው ነገር የለም። በሌላ በኩል ለሁለት ዓመታት በሰሜን ኢትዮጵያ በነበረው ጦርነት ተሳታፊ የነበሩት የኤርትራ ወታደሮች ከሽረ እና ከአክሱም ለቀው ወደ ድንበር አቅጣጫ በመሄድ ላይ ናቸው ሲል ሮይተርስ የዓይን እማኞቹን ጠቅሶ ከሳምንት በፊት ዘገባ ማስነበቡ ይታወሳል።

/ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

XS
SM
MD
LG