በኢትዮጵያ የጥምቀት ከተራ በኦኣት በተለያዩ ቦቻዎች ተከብሯል። በዓሉ ከክርስቶስ የጥምቀት መታሰቢያነት ባለፈ የሰው ልጆች ትህትናን እና መከባበርን የሚማሩበት እንደሆነ የእምነቱ ተከታዮች እና የኃይማኖት አባቶች ተናግረዋል፡፡
በሌላ በኩል በሰሜን ኢትዮጵያ ለሁለት ዓመታት ከተካሄደው ጦርነት በኋላ ጥምቀት በድምቀት ከሚከበርባቸው ስፍራዎች መሃከል አንዷ በሆነችው ጎንደር በመቶ ሺሆች የተቆጠሩ እንግዶችን መቀበሏን የከተማዋ ኮምዩኒኬሽን አስታውቋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማም በተመሳሳይ የከተራ በዓል ኃይማኖታዊ ስርዓትን በተከተለ መልኩ በድምቀት ተከብሯል፡፡ ታቦታትም ከደብሮቻቸው ወደ ማደሪያቸው አምርተዋል፡፡
/ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/