በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዛሬ ማለዳ በፖሊስ ከቤቱ የተወሰደው ተመስገን ደሳለኝ ቀትር ላይ ከእስር እንደተፈታ ገለጸ


ዛሬ ማለዳ በፖሊስ ከቤቱ የተወሰደው ተመስገን ደሳለኝ ቀትር ላይ ከእስር እንደተፈታ ገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:03 0:00

የፍትሕ መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ተመስገን ደሳለኝ፣ በዛሬ ዕለት፣ ከማለዳ ጀምሮ እስከ እኩለ ቀን ድረስ ታስሮ መፈታቱን፣ ለአሜሪካ ድምፅ ገለጸ፡፡

ዛሬ ማክሰኞ፣ ማለዳ 12 ሰዓት ተኩል ገደማ፣ ሲቪል የለበሱ ፖሊሶች፣ ከመኖሪያ ቤቱ መጥተው እንደወሰዱት የተናገረው ተመስገን፣ የታሰረበት ምክንያት፣ ከዚህ ቀደም በከፍተኛ ፍርድ ቤት ውድቅ ከተደረጉ ሦስት ክሦች መካከል በሁለቱ ላይ እንዲከላከል፣ በዐቃቤ ሕግ በቀረበው ይግባኝ መሠረት፣ “ጠቅላይ ፍርድ ቤት መቅረብ ሲገባው፣ በተደጋጋሚ በነበሩ ቀጠሮዎች ባለመገኘቱ፣ ታስሮ እንዲቀርብ በመወሰኑ” እንደኾነ፣ ከፖሊስ እንደተነገረው አስረድቷል፡፡

ይሁን እንጂ፣ ይግባኝ ስለመባሉም ይኹን መጥሪያ ስለ መጻፉ፣ ከዛሬ በፊት የሚያውቀው ነገር እንደሌለ ተናግሯል፡፡የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ መጥሪያ፣ እርሱ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት እያለ፣ ጥቅምት 21 ቀን 2015 ዓ.ም. መጻፉን ያወቀው፣ ዛሬ በፖሊስ በታሰረበት ወቅት እንደኾነ የገለጸው ተመስገን፣ መጥሪያውን ተቀብሎ መለቀቁን አመልክቷል፡፡ በቀጣዩ ወር ሐምሌ 7 ቀን 2015 ዓ.ም. ጠቅላይ ፍርድ ቤት እንደሚቀርብም ተናግሯል፡፡ በጉዳዩ ላይ ከፖሊስ ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

ተመስገን ደሳለኝ ከኬኔዲ አባተ ጋራ ያደረገው አጭር ቆይታ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

XS
SM
MD
LG