በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሦሪያና አሜሪካ በዓለምአቀፍ መድረኮች







please wait

No media source currently available

0:00 0:07:34 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በሁለተኛይቱ የሩሲያ ግዙፍ ከተማ ሳንክት ፒተርቡርግ ውስጥ ለሚካሄደው የሃያዎቹ በምጣኔ ኃብት የተራመዱ ሃገሮች ስብሰባ ለመገኘት ወደዚያው ሲያመሩ ዛሬ እግረመንገዳቸውን ስዊድን ጎራ ብለዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ዛሬ ከስዊድኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይን ፌልድት ጋር ሆነው በሰጡት መግለጫ የሦሪያ የኬሚካል ጥቃት አፀፋ ካልተሰጠው የዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ተዓማኒነት ጥያቄ ውስጥ እንደሚገባ አስጠንቅቀዋል፡፡

ሚስተር ኦባማ የሦሪያው ፕሬዚዳንት ባሻር አል አሳድ አልፈውታል የተባለውን ቀይ መስመር ያሰመሩት እርሣቸው አለመሆናቸውን፣ ይልቅ ቀደም ሲል ሃገሮች በደረሱበት ውሣኔና በፈረሙት ስምምነት መሠረት ዓለም መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

“ሶሪያ ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ኋላቀር እና አረመኔአዊ አድራጎት በዝምታ ላለመመልከት እኔና የስዊድኑ ጠቅላይ ሚነስትር ተስማምተናል” ብለዋል ሚስተር ኦባማ በዚሁ መግለጫቸው፡፡

የፈረንሣይ ፕሬዚዳንት ፍራንሷ ኦላንድ ለፕሬዚዳንት ኦባማ የወታደራዊ እርምጃ ሃሣብ ያላቸውን ድጋፍ አሳውቀዋል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ባን ኪ-ሙን ደግሞ ወደ ሦሪያ የተላከው ፈታሽና መርማሪ ቡድን ሪፖርት ሳይሰማ አንዳችም ወታደራዊ እርምጃ እንዳይወሰድ አሳስበዋል፡፡

የጂ ሃያው ጉባዔ ዋነኛ ትኩረት ሦሪያ ሳትሆን አትቀርም ተብሎ የተገመተ ሲሆን በሕዝባቸው ላይ ጅምላ ጨራሽ መርዝ ጋዝ ተኩሰዋል ባሏቸው የፕሬዚዳንት ባሻር አል አሳድ ይዞታዎች ላይ ወታደራዊ ጥቃት ለማድረስ እየተዘጋጁ ያሉት ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ከጉባዔው ጎን ለጎን በሚያደርጓቸው የተናጠል ስብሰባዎች ዓለምአቀፍ ድጋፍ ለማሰባሰብ ጥረት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የሦሪያ መንግሥት ነኀሴ 15/2005 ዓ.ም የተጣለውንና ከአራት መቶ በላይ ሕፃናትን ጨምሮ ከሺህ በላይ ሰው የገደለውን ሳሪን የሚባል የመርዝ ጋዝ ጥቃት ያደረሰው እርሱ አለመሆኑን እየገለፀ ነው፡፡

ለተጨማሪና ዝርዝር የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG