በተመድ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ-ግሪንፊልድ ከዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ ጋር በዚህ ሳምንት ተገናኝተው ነበር። ዩናይትድ ስቴትስ እአአ የካቲት 24 ቀን በሩሲያ ለተወረረቸው ዩክሬን ያላትን የማይናወጥ ድጋፍ ለዜሌንስኪ እንደገለጹላቸው ግሪንፊልድ ተናግረዋል።
ቶማስ-ግሪንፌልድ ከቪኦኤ የምሥራቅ አፍሪካ ሃላፊ ማይሮስላቫ ጎንጋዥ ጋር በዋርሶ ረቡዕ ዕለት ቆይታ አድርገዋል።
/ቀጣዩ ቃለ መጠይቅ ትክክለኛ ቃላትን ለመጠቀምና ግልጽ ለማድረግ ሲባል አርትኦት ተደርጎበታል።/