በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአማራ ክልል በጦርነቱ ምክኒያት 28 ሺሕ ለአዕምሮ መታወክ ተዳርገዋል ተባለ


በአማራ ክልል በጦርነቱ ምክኒያት 28 ሺሕ ለአዕምሮ መታወክ ተዳርገዋል ተባለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:24 0:00

ጦርነት በተካሄደባቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች ውስጥ ከ28 ሺሕ ሕዝብ በላይ ለዓዕምሮ መታወክ ሊጋለጥ እንደሚችል የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ። የችግሩ ሰለባዎች በአብዛኛው ህጻናትና ሴቶች ናቸው ተብሏል።

በክልሉ ጤና ቢሮ የእቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ክፍል ዳይሬክተር ሞገስ አስረሴ የችግሩ ሰለባዎች ቁጥር ከተጠቀሰው ከፍ ሊል እንደሚችል ጠቁመዋል። ኅብረተሰቡ ወደ ጤና ተቋም የመሄድ ባህሉ አናሳ መሆን፣በአካባቢቸው አደሎና መገለል ይደርስባናል የሚል ስጋት መያዛቸውና በሌሎች ምክኒያቶች ወደ ሕክምና ተቋም የሚሄዱ ሰዎች ቁጥር አነስተኛ መሆኑን ተናግረዋል።

ከጦርነቱ ጋር ተያይዞ የጤና እና የሥነ ልቦና ችግር ያጋጠማቸውን ሰዎች ሕክምና ምክር በመስጠት ላይ የሚገኘው የደሴ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆሰፒታል ሥራ አስኪያጅ ዶክተር አየለ ኃይማኖት በተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን በኩል የሥነ ልቦና ባለሞያ ተመድቦ በአገልግሎት ለመስጠት ቢሞከርም ከደረሰው ጉዳት አሳሳቢነት አንጻር ሆስፒታሉ በሚችለው ልክ እንዳልተንቀሳቀሰ ተናግረዋል።

XS
SM
MD
LG