ዋሺንግተን ዲሲ —
የፓኪስታን ባለሥልጣናት በዩናይትድ ስቴትስ የሚፈለጉትንና እኤአ በ2008 ሕንድ ሙምባይ ከተማ ላይ 168 ሰዎች የተገደለበት ጥቃት ዋና አቀናባሪ ተብለው የተወነጀሉ ፅንፈኛ የሃይማኖት መሪ ለቀቁ።
ፓኪስታን ውስጥ ያስቻለው ፍርድ ቤት የሀገሪቱ መንግሥት የሃፌዝ ሳኢድን የቁም እሥር ፍርድ በሦስት ወር እንዲያራዝም ያቀረበውን ጥያቄ ውድቅ አድርጎ ለቋቸዋል። ፍርድ ቤቱ የለቀቃቸው መንግሥቱ ለመሠረተው የሽብርተኝነት ክስ በቂ ማስረጃ አላቀረበም የሚል ምክንያት ሰጥቷል።
የዩናይትድ ስቴትስ የፍርድ ሚኒስቴር ሃፊዝ ሳኢድን በሽብርተኝነት ፈርጆ እንዲያዙ ወይም እንዲገደሉ ለሚያደርግ የአሥር ሚሊዮን ዶላር ወሮታ መድቧል።
ሳኤድን ፍርድ ቤቱ ከቁም እሥር የለቀቃቸው ዛሬ ዓርብ ንጋት ላይ ነው።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ