በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ከፍተኛ የመብት ጥሰት እየደረሰብን ነው፤ የሚል ስሞታ በተደጋጋሚ ሲያሰሙ ቢቆዩም፤ በክልሉ ፕሬዝዳንት ትዕዛዝ በልዩ ፖሊስ አማካኝነት ይፈጸሙብናል ያሏቸው በደሎች ይበልጥ ተባብሰው ቀጠሉ እንጂ ማብቂያ አልተበጀላቸውም፤ ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ይከሳሉ።
ይሄንኑ ቅሪታቸውን ይዘው ሰሞኑን ወደ አዲስ አበባ ያቀኑት ያካባቢው ያገር ሽማግሌዎችና የጎሳ ተጠሪዎች አቤቱታቸውን ካሰሙባቸው የፌድራል ባለ ሥልጣናት ምላሽ በመጠባበቅ ላይ ሳሉም፤ “ይህን ክስ ይዛችሁ ለምን ወደዚያ ሄዳችሁ” በሚል በቤተሰቦቻችን ላይ ተጨማሪ ጥቃት እየተፈጸመ ነው፤ ሲሉ ለአሜሪካ ድምጽ ገልጠዋል።
በክልሉ በክልሉ ፕሬዝዳንት የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተፈጸምብን ነው የሚለውን ይሕን የነዋሪዎቹን ክስ ባማጣራት ላይ መሆኑ የገለጸው መንግስታዊው የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮምሽን በበኩሉ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ኮምሽነር ራሳቸው ድብደባ የተፈጸመባቸው መሆኑን አመልክቷል። አጣርቼ ለተወካዪዮች ምክር ቤት ሪፖርት አቀርባለሁ ይላል።
የዘገባውን ሙሉ ዝርዝር ከዚህ ያድምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ