በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአልጀሪያ የጦር አውሮፕላን ተከስክሶ 257 ተሣፋሪዎች ሕይወታቸው አለፈ


አንድ የአልጄሪያ ወታደራዊ ማጓጓዣ አውሮፕላን ዛሬ ወድቆ በትንሹ 257 ተሣፋሪዎቹ ማለቃቸውን የሃገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።

አንድ የአልጄሪያ ወታደራዊ ማጓጓዣ አውሮፕላን ዛሬ ወድቆ በትንሹ 257 ተሣፋሪዎቹ ማለቃቸውን የሃገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ባለሥልጣናት በገለፁት መሠረት አውሮፕላኑ ከተነሳ ጥቂት ጊዜ በኋላ የወደቀው ከዋና ከተማዋ ከአልጀርስ ደቡብ ምዕራብ 25 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከሚገኘው ከቡፋሪቅ ጦር ሠፈር አቅራቢያ ነው።

ከሰላባዎቹ መካከል 247ቱ ተሳፋሪዎች ሲሆኑ አሥሩ የአውሮፕላኑ ሠራተኞች ናቸው ተብሏል።

ማንነታቸውን ለመለየት አስከሬኖቻቸው ወደ ኤን ናደጃ ወታደራዊ ሆስፒታል ተወስዶ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን የመከላከያ ሚኒስቴሩ ጨምሮ ገልጿል።

አውሮፕላኑ የወደቀበት ምክንያት ምን እንደሆነ ወዲያውኑ የተሰጠ መግለጫ ግን የለም።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG