ዓለማየሁ እሸቴ ትናንት አረፈ። የሚሊዮኖችን ቀልብ ከሳቡ ድምፃዊያን አንዱ ዓለማየሁ የኪነጥበብ አስተዋጽዖዎችና ሥራዎች እየታውሱ ነው።
ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ ኀዘናቸውን ገልፀዋል። ለዓለማየሁ እሸቴ በቅርቡ "የላቀ አስተዋፅዖ ሽልማት" ያበረከቱለት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ “ሥራዎቹ ኢትዮጵያን ከፍ እንዳደረጉ ይኖራሉ” ብለዋል።
አንጋፋው የኪነጥበብ ባለሙያ ደበበ እሸቱ አለማየሁን "ከዓለምአቀፍ ባለሙያዎች ጋር የሚነፃፀር" ብሎታል።
ሌላው አንጋፋ የኪነጥበብ ሰው እና የቀድሞው የፖሊስ ኦኬስትራ ባልደረባው ተስፋየ አበበ "ድፍረት የሚጠይቁ ሥራዎችን የሠራ ጀግናና ሕዝባዊ አርቲስት" ሲሉ አሞካሽተውታል።
ዓለማየሁ እሸቴ በቅርቡ በአሜሪካ ድምፅ ያስተላለፈውን መልዕክት ከተያያዘው የቪድዮ ክሊፕ ይመልከቱ።