በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የራያ አላማጣ አስተዳደር ትግራይ ክልልን በጦርነት ቀስቃሽነት ከሰሰ


የራያ አላማጣ አስተዳደር ትግራይ ክልልን በጦርነት ቀስቃሽነት ከሰሰ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:40 0:00

የራያ አላማጣ አስተዳደር ትግራይ ክልልን በጦርነት ቀስቃሽነት ከሰሰ

በራያ አላማጣ ወረዳ የተለያዩ ቦታዎች ውጊያ ከፍተዋል ያላቸው የትግራይ ክልል ታጣቂዎች፣ አብዛኛውን የወረዳውን አካባቢዎች በኀይል ተቆጣጥረዋል፤ ሲል የወረዳ አስተዳደሩ ከሰሰ።

የአላማጣ ከተማ ከንቲባ አቶ ኀይሉ አበራ፣ ከሚያዚያ 3 ቀን 2016 ዓ.ም. እስከ ዛሬ ባሉት ቀናት ውስጥ፣ ከትግራይ ክልል ተነሥተዋል ያሏቸው የታጠቁ ኀይሎች በሰነዘሩት ወታደራዊ ጥቃት፣ ያልታጠቁ ሰዎች ላይ የሞት እና የአካል ጉዳት መድረሱን ገልጸዋል።

የደቡብ ትግራይ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሃፍቱ ኪሮስ በበኩላቸው፣ የተጋነነ ግጭት እንደሌለ ጠቅሰው፣ ይህም ቢኾን ከራያ አላማጣ ወረዳ ትንኮሳ በመቀስቀሱ የተፈጠረ ነው፤ ብለዋል።

ማምሻውን ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጡ የአላማጣ እና የኮረም ነዋሪዎች ግን፣ በጸጥታው ስጋት ምክንያት ከተሞቹን ለቀው የወጡ ሰዎች ስለመኖራቸው አመልክተዋል።

ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG