በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የድሬዳዋ ምድብ ችሎት የአልሻባብ አባላት በተባሉ ተከሳሾች ላይ የቅጣት ውሳኔ አስተላለፈ


በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የድሬዳዋ ምድብ ችሎት የጂጂጋ ተዘዋዋሪ ችሎት በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በ4 መዝገቦች የተከሰሱ 88 የአልሸባብ አባላት ናቸው የተባሉ ተከሳሾች ላይ እስከ 20 ዓመት የሚደርስ እሥራት ፍርድ አስተላልፏል።

ተከሳሾቹ በ2014 ዓም እና በ2015 ዓ/ም የጸጥታ አካላትና ሰላማዊ ሰዎች ላይ ጉዳት በማድረስ፣ ከ13 ሚሊዮን ብር በላይ ንብረት በመዝረፍና በማውደም እንዲሁም መንግሥታዊ መረጃዎችን ለአልሸባብ የሽብር ቡድን አሳልፈው በመስጠት የተከሰሱ መሆናቸው ታውቋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG