በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአልሸባብ ታጣቂዎች በኬንያ ምሥራቃዊ ክፍል 4 ሰዎች ገደሉ


ዛሬ ኬንያ ሰሜን ምስራቃው ክፍለ ግዛት ውስጥ ተጠርጣሪ የአልሸባብ ታጣቂዎች በአንድ አውቶቡስ ላይ ተኩስ ከፍተው አራት ሰው መግደላቸውን የኬንያ የፀጥታ ባለሥልጣን አረጋገጡ።

የሶማሊያ እስላማዊ ነውጠኛው ቡድን ኬንያ ሶማሊያ ውስጥ ወታደሮችዋን በማስገባትዋ ለመበቀል በአካባቢው በአውቶቡሶች እና ሌሎችም ተሽከርካሪዎች ላይ በተደጋጋሚ ጥቃት ያደርሳል።

የዛሬው ጥቃት የደረሰው አውቶቡሱ ከማንዴራ ወረዳ ወደ ናይሮቢ በመጉዋዝ ላይ እንዳለ መሆኑ ነው የተገለጸው። ማንዴራ በስተሰሜን ከኢትዮጵያ በስተምሥራቅ ደግሞ ከሶማሊያ ጋር ትዋሰናለች።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG