ከኢትዮጵያ ጋር በድንበር በምትዋሰን አንድ የሶማሊያ ከተማ ላይ ዛሬ የአልሻባብ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት 10 ሰዎች መገደላቸውን እና ከ20 በላይ መቁሰላቸውን የአካባቢው ባለሥልጣናት እና የዐይን እማኞች ተናገሩ።
በሌላ በኩል ወደ ኢትዮጵያ ሰርጎ ለመግባት የሞከረውን የአልሸባብ የሽብር ቡድን መደምሰሱን የመከላከያ ኃይል ስምሪት ኃላፊና ጊዜያዊ የፀጥታ ኮማንድ ፖስት አስተባባሪ ሜጀር ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው ለአገር ውስጥ መገናኛ ህዝብ ተናግረዋል።
/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ/