ሜልቦርን - አውስትራሊያ —
ከትናንት በስተያ፣ ዕሁድ - ሐምሌ 13/2006 ዓ.ም አውስትራሊያ - ሜልቦርን ከተማ ላይ የተከፈተው ሃያኛው የዓለም የኤድስ ጉባዔ ዛሬ የሁለተኛ ቀን የሙሉ ቀን ውሎውን አጠናቅቋል፡፡
እስከፊታችን ዓርብ በሚዘልቀው የሜልቦርኑ ጉባዔ ላይ ከሚቀርቡት ጥናታዊ ፅሁፎች፣ ማኅበራዊ ሪፖርቶች፣ የጎን ውይይቶች፣ የዓለም መንደር ዝግጅቶችና የፖስተር ትርዒቶች በተጨማሪ የተለያዩ የፈጠራ ውጤቶች፣ የቪድዮ ቅንብሮችና ሌሎችም ይወጣሉ፤ ይታያሉ፡፡
“ሣይንስ ብቻውን መፍትሔ አይደለም” በተባለበት በዚህ ጉባዔ ላይ ዓለም ከኤድስ ጋር የተያያዘ ማግለልና ማሸማቀቅን አበርትቶ መታገል እንዳለበት ተነግሯል፡፡
“Living in the Shadow” – (ተደብቆ መኖር) በሚል ርዕስ በአሜሪካ ድምፅ - ቪኦኤ የተዘጋጀ ጥናታዊ ፊልም ትናንት ለመጀመሪያ ጊዜ ታይቷል፡፡
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡