በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሦስት ዓለም ዓቀፍ ግብረሰናይ ድርጅቶች ታገዱ


ፎቶ ፋይል፦ መቀሌ
ፎቶ ፋይል፦ መቀሌ

የፌደራል መንግሥቱ ሦስት ዓለም አቀፍ ግብረሰናይ ድርጅቶች ለሦስት ወራት ኢትዮጵያ ውስጥ የሚያደርጓቸውን እንቅስቃሴዎች ለ3 ወራት እንዲያቆሙ መወሰኑን አስታውቋል።

ለ6 ቀናት በኢትዮጵያ ጉብኝት ሲያካሂዱ የቆዩት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮችና የድንገተኛ እርዳታ አስተባባሪ ማርቲን ግሪፊት የረድዔት ድርጅቶችን በአድሏዊነት መክሰስ አደገኛ ነው ብለዋል። በሌላ በኩል ትላንት ሐምሌ 27 ቀን 157 ሰብዓዊ እርዳታን የያዙ የጭነት መኪናዎች መቀሌ መግባታቸው የተገለጸ ሲሆን ማርቲን ግሪፊት ሰብዓዊ ድጋፍን በተመለከተም በመግለጫቸው አንኳር መረጃዎችን አንስተዋል።

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ በትግራይ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 3 ዓለም ዓቀፍ ግብረሰናይ ድርጅቶች የመጨረሻ ውሳኔ እስኪሰጣቸው ድረስ ለሦስት ወራት በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ እንዲያቋርጡ አዟል። እገዳው የተላለፈባቸው የሆላንድ ድንበርየለሽ የሀኪሞች ቡድን (MSF Holland)፣ የኖርዌይ ተፈናቃዮች ምክርቤት (Norwegian refugee council) እና አልማክቶም ግብረሰናይ ድርጅት (Al Maktom Foundation) ናቸው።

ሦስቱም ድርጅቶች የሥራ ፈቃድ ያልተሰጣቸውን የውጭ ሃገር ዜጎች ወደሃገር ውስጥ አስገብተው ከ6 ወር በላይ ቀጥረው በማሰራት የተከሰሱ ሲሆን የሆላንድ ድንበርየለሽ የሀኪሞች ቡድንና የኖርዌይ ተፈናቃዮች ምክርቤት ሃሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨት ተከሰዋል፣ የሆላንዱ ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን በተጨማሪ ፈቃድ ያልተሰጣቸውን የሳተላይት የሬዲዮ መገናኛ መሳሪያዎችን ወደሃገር ውስጥ በማስገባት የድርጅቱ ሰራተኞች “አፍራሽ” ለሆነ አላማ ሲጠቀሙበት እና ይዘው ሲንቀሳቀሱ እጅ ከፍንጅ በመያዛቸው የተከሰሰ ሲሆን አል ማክቶም ግብረሰናይ ድርጅት ደግሞ ከበጀት አጠቃቀምና የሰራተኞች አስተዳደር እንዲሁም ከኮቪድ 19 ጥንቃቄ ጋር የተያያዙ ችግሮች እንደታዩባቸው የኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች መረጃ ማጣሪያ መግለጫ ያመለክታል።

በትላንትናው ዕለት ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮችና የድንገተኛ እርዳታ አስተባባሪ ማርቲን ግሪፊት ግን በረድዔት ድርጅቶች ላይ ለህወሓት ያዳላሉ በሚል እየቀረበ ነው ያሉትን ክስ “አደገኛ” ብለውታል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ሦስት ዓለም ዓቀፍ ግብረሰናይ ድርጅቶች ታገዱ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:41 0:00


XS
SM
MD
LG