በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካ ህብረት የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ በመቻቻልና ንግግር እንዲፈታ ጥሪ አቀረበ


የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ደላሚና ዙማ
የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ደላሚና ዙማ

የአፍሪካ ህብረት ኢትዮጵያ ውስጥ የተፈጠረው ሁኔታ በመቻቻል እንዲያዝና ንግግሮች እንዲደረጉ ጥሪ አቀረበ።

የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ኒኮሳዛና ላሚኒ ዙማ ባለፉት ጥቂት ወራት ኢትዮጵያ ውስጥ እየተፈጠሩ ያሉትን ማህበራዊና ፖለቲካዊ ሁኔታዎች በከፍተኛ ስጋት እየተከታተሉ መሆኑን ገልጸዋል።

በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የእርሻ መሬት ለልማት ከተመደበበት ዕቅዶች በተያያዘ በተፈጠረው ውዝግብ ምክንያት የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች መከሰታቸውን ተከትሎ የብዙ ሰው ሕይወት መጥፋቱ ተዘግቧል ያለው የአፍሪካው ህብረት መግለጫ የመንግስትና የግል የንግድ ሥራዎች አልፎ አልፎም የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎቶች የተቋረጡበት ሁኔታ መፈጠሩን አመልክቷል።

የህብረቱ ሊቀ-መንበር ዙማ ለሞቱት ሰዎች ቤተሰቦች ሃዘናቸውን በመግለጽ የቆሰሉትም በቶሎ ጤናቸውን እንዲያገኙ ምኞታቸውን ገልጸዋል።

ለተቃውሞዎቹ መነሾ የሆኑት ማህበራዊ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ሰላማዊ እና ዘላቂ መፍትሄ ለማግኘት እንዲቻል የሚመለከታቸው ወገኖች ሁሉ እንዲነጋገሩ የተማጸኑት ዙማ በሀገሪቱ በከፍተኛ ደረጃ ቁጥብነትና መረጋጋት እንዲሰፍን ጥሪ አድርገዋል።

አያይዘውም የአፍሪካ ህብረት ለዲሞክራሲ ባህልና መርሆች ወሳኝ የሆኑት የህግ የበላይነት እና በሰላማዊ መንገድ የመሰለፍ መብት እንዲከበር የሚደግፍ መሆኑን የህብረቱ ሊቀመንበር አረጋግጠዋል።

XS
SM
MD
LG